
በመኮንን ተሾመ ቶሌራ
የምርምር ስራዎች በጥንቃቄ እና በስነምግባር ካልተሰሩ በአካባቢ ፣ በእንስሳትና በመላዉ የሰዉ ልጆች ላይ ከፍተኛ ጥፋት ሊያስከትሉ ይችላሉ።
ይሁንና ተመራማሪዎች ፣ ሳይንቲስቶችና የፖለቲካ አመራሮች በማወቅም ሆነ ባለመማቅ የምርምር ስነምግባር መርሆች ከሚያዙት በተቃራኒ አሳዛኝ ጥፋቶችን ሲያደርሱ ይታያሉ። በመሆኑም ለምርመር ስራ የሚሆኑ የስነምግባር መመሪያዎችን ማዉጣትና መመሪያዎቹ እንዲከበሩ መስራት የመንግስታትና የተቋማት ስራ ከሆነ ዉሎ አድሯ።
በምርምር ዙሪያ የሚፈፀሙ ቸልተኝነቶች የአካባቢ ዉድመትን ፣ የሰዉና የእንስሳት ጤና መጉዳትንና የትምህርት ጥራትን ጨምሮ ከፍተኛ ማህበራዊ ጥፋቶችን እንደሚያስከትሉ እሙን ነዉ። ከዚህ አንፃር በርካታ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል።
“የሲኦል ዶክተሮች”
ከምርምር ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሱ ጥፋቶችን በተመለከተ በርካታ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል። ለአብነትም የ 2ኛዉ የአላም ጦርነትን ተከትሎ ቪቪን ስፒትስ የተባለችዉ የ22 ዓመቷ የፍርድ ቤት ዉሎ ዘጋቢ በኑረምበርግ ከተማ የናዚ ዶክተሮች ያደረጉትን አሰቃቂ የህክምና ሙከራዎች አስመልክታ “የሲኦል ዶክተሮች ፡ በሰዎች ላይ የተደረገዉ የናዚዎች አሰቃቂ የህክምና ሙከራዎች ዘገባ” በሚል በፃፈችዉ ታሪካዊ ፅሁፍ በሰዉ ልጅ ታሪክ ስለተፈፀመዉ ዘግናኝ የህክምና ባለሙያዎች ወንጀል በግልፅ ፅፋለች።
የ 2ኛዉ የአላም ጦርነትን ተከትሎ ቪቪን ስፒትስ የተባለችዉ የ22 ዓመቷ የፍርድ ቤት ዉሎ ዘጋቢ በኑረምበርግ ከተማ የናዚ ዶክተሮች ያደረጉትን አሰቃቂ የህክምና ሙከራዎች አስመልክታ “የሲኦል ዶክተሮች ፡ በሰዎች ላይ የተደረገዉ የናዚዎች አሰቃቂ የህክምና ሙከራዎች ዘገባ” በሚል በፃፈችዉ ታሪካዊ ፅሁፍ በሰዉ ልጅ ታሪክ ስለተፈፀመዉ ዘግናኝ የህክምና ባለሙያዎች ወንጀል በግልፅ ፅፋለች።
በወቅቱ በናዚ መሪዎች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ዶክተሮች በማጎሪያ ካምፖች የነበሩ እስራኤላዊ አይሁዶችን ጨምሮ እስረኞችን እስከ 68,000 ጫማ ድረስ በሚስተካከሉ የከፍታ ቦታዎች ቆይታ “high-altitude experiments” የሙከራ ስፍራዎች በማጎር ያለ አየር⁄ ኦክስጅን ⁄ ለረጅም ሰአታት እንዲቆዩ በማድረግ የሰዉ ልጅ እስከምን ድረስ በከፍታ ቦታዎች ሊቆይ እንደሚችል ጥናት ያደርጉባቸዉ ነበር ፣ ከሌሎቹ ደግሞ ከጭኖቻቸዉና ከሙሉ እግሮቻቸዉ አጥንት በመንቀል እየወሰዱ ወደ ሌሎች ተጎጂዎች የመትከል ሙከራ ሲያደርጉ ፣ የጡንቻ እና የነርቮች ክፍሎችን ማስወገድ ፣ የሰው ሰራሽ መቁሰል እና ለሰናፍጭ ጋዝ ማጋለጥ ፣ሁለት እግሮቻቸዉን ሆን ብሎ በማቁሰል እና አንዱን ግን በ sulfanamide አንቲባዮቲክ መድኃኒቶች በማከም ፣ ትኩስ ታይፈስ ያለበት ጡንቻ ውስጥ የመርፌ መድሃኒትን መሞከርና እና 112 አይሁዳውያን እስረኞች ላይ ደግሞ በህይወት እያሉ አጥንቶቻቸዉን በማዉጣት በጦርነት ለተጎዱ የራሳቸዉ ዜጎች ንቅለ ተከላ ለማድረግ መሞከርና በመጨረሻም አይሁዳውያኑን የመገደል ተግባር በመፈፀም በአለማችን የህክምን ታሪክ ዉስጥ የማይረሳ ጠባሰ ጥለዉ አልፈዋል።
የሄልሲንኪ ስምምነት ⁄ Helsinki Declaration⁄
የሄልሲንኪ ስምምነት የናዚዎችን አሰቃቂ የህክምና ሙከራዎች ተከትሎ የመጣ ለህክምና ምርምር አለም አቀፍ የስነምግባር መርሆዎችን የያዘ ስምምነት ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ ለሳይንሳዊ ጥረቶች መሰረት ይሰጣል። በህክምና ምርምር ውስጥ የሚሳተፉትን ለራሳቸው ጥቅም እና ሌሎች ተመሳሳይ የጤና እክል ያለባቸውን ሰዎች ይጠብቃል።
በሄልሲንኪ ስምምነት ላይ የተዘረዘሩት የሥነ-ምግባር መርሆዎች እና ጥበቃዎች የሕክምና ምርምር ለሁሉም በተቻለ መጠን ጥሩ ውጤት በሚያስገኝ መንገድ መደረጉን ያረጋግጣሉ።
የሄልሲንኪ ስምምነት በሰዎች ላይ የሥነ-ምግባር ሕክምና ምርምር መመሪያ ይሰጣል። መጀመሪያ ላይ በሰኔ 1964 በሄልሲንኪ ፊንላንድ በተደረገው 18ኛው የአለም የህክምና ማህበር ጉባኤ ተቀባይነት አግኝቷል።
የሄልሲንኪ ስምምነትለመጀመሪያ ጊዜ በ 1947 በኑረምበርግ ኮድ ውስጥ ከተገለጹት 10 መርሆዎች ተዘጋጅቷል ። ከጄኔቫ ስምምነት (እ.ኤ.አ. በ 1948 የተደረገ) የሐኪሞች የሥነ ምግባር ግዴታዎች መግለጫ ተጨማሪ አካላትን አካቷል ።

ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የተደረገ የቂጥኝ በሽታ ሙከራ
እ.አ.አ በ1932 የዩ.ኤስ አሜሪካ የህብረተሰብ ጤና አገልግሎት (USPHS) 600 የቱስኬጊ አላባማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ጥቁር አፍሪካውያን አሜሪካውያን ወንዶችን በፕሮጀክት በመመዝገብና የነጻ የሕክምና አገልግሎት ተስፋ በመስጠት ህክምና ላልተገኘለት ለቂጥኝ በሽታ መፍትሄ ለማፈላለግ የበሽታዉን ባክቴሪያ በመዉጋት ጥናቱን ጀመረ።
የጥናቱ ዋነኛ አላማም ያልታከመ የቂጥኝ ባክቴሪያ እድገትን ታሪክ ለመከታተል ነበረ። ነገር ግን ተመራማሪዎቹ በወቅቱ ለጥናቱ ተሳታፊዎች ሙሉ መረጃ በመስጠት ፈቃደኝነትና ስምምነት አላገኙም ነበር። በተሳታፊዎቹ ላይም ምርምር ካካሄዱ በኋላም ህክምና አልሰጡአቸዉም። ይሁንና Ad Hoc Advisory Panel ሀሳብ ጥናቱ በ1972 ተጠናቀቀ። ይህ በጥቁር አሜሪካዉያን ላይ የተሰራዉ የተሳሳተ የጥናት ሁኔታ በዜና ዘገባዎች ከታተመ በኋላ በጤና እና ሳይንሳዊ ጉዳዮች ረዳት ጸሐፊ ፓኔሉን ሊጠራ ችሏል።
በኋላም እ.ኤ.አ. በ 1997 ፕሬዚደንት ክሊንተን በጉዳዩ ዙሪያ ለአሜሪካ ህዝብ ፕሬዚደንታዊ ይቅርታ አቅርበዋል ። በወቅቱም ከይቅርታቸዉም ጋር አያይዘዉ እንደዛ ያለ ስህተት እነዳይደገም በቱስኬጊ ዩኒቨርሲቲ የባዮኤቲክስ የምርምር እና የጤና እንክብካቤ ብሔራዊ ማዕከልን ለማቋቋም የሚያስችል ኢንቬስት ማድረጉን አስታውቀዋል። ይህንን ታሪካዊ የህክምና ስህተት በተመለከተም ለአሜሪካ ብዙ መዝገቦች በብሔራዊ ቤተ መዛግብት ውስጥ ይገኛሉ።
የቤልሞንት ሪፖርት The Belmont Report
የቤልሞንት ሪፖርት የሰዉ ልጆች ላይ ምርምር ለማካሄድ የሚያስችሉ የስነምግባር መርሆዎችን ይዘረዝራል። እንዲሁም የሰው ልጆችን የጤና ደህንነት ለመጠበቅ የአሜሪካ ደንቦችን ያቀርባል። የቤልሞንት ሪፖርት የተፃፈው በ1979 በብሔራዊ የባዮሜዲካል እና የባህርይ ምርምር ዋና ዋና ጉዳዮች ጥበቃ ኮሚሽን ነው። ኮሚሽኑ የተመሰረተዉ እ.አ.አ በ1974 በወጣው የብሔራዊ ጥናትና ምርምር ህግ መሰረት ነው። ዋና አላማዉም እንደ ቱስኬጊዉ ላሉ በምርምር ውስጥ ለሚፈጸሙ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ ምላሽ በመስጠት ነዉ።
የሄሮፊለስ ⁄ Herophilus ⁄ ዘግራኝ የምርምር ስነምግባር
ከ 335 እስከ 280 አመተ አለም በግብፅ አሌእሳነደሪያ የኖረዉን የግብፃዊዉ የሄሮፊለስን የሰው ልጆችን እንደ ከብት መበለትና መመራመር ጨምሮ በረካታ ዘግራኝ የምረመር ስነምግባር ስተቶች ታይተዋል።
ሄሮፊለስ Herophilus በግብፅ አሌክሳንድሪያ ውስጥ የሕክምና ስራ ይሰራ የነበረ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ቶለማዮ ፋሮአስ የግዛት ዘመን ከግሪኩ ሐኪም እና አናቶሚስት ኢራስትራተስ ጋር በመሆን ቢያንስ ከ 30 እስከ 40 ዓመታት ያህል የሰውን አካል ለመበተን ተፈቅዶለት ነበር።
በቶለሚ 1ኛ እና በቶለሚ 2ኛ ስር ወንጀለኞች እንዲበለቱ እና እንዲገለሉ ቅጣት ሲፈረድባቸዉ ነበር ። በዚህም ወደ 600 በሚገመቱ እስረኞች ላይ የመበለት የጭካኔ ስራ በማከናወን ወደር የሌለዉ ታሪካዊ ጥፋት አድርሷል።
ከዚህ በተጨማሪ የሲአይኤ የአእምሮ መቆጣጠሪያ ሙከራዎች (Project MK-Ultra)፣ የስቴትቪል እስር ቤት የወባ ጥናት ፣
የ1939 ኙ ጭራቃዊ ጥናት እና ሌሎች በርካታ ስነምግባር የጎደላቸዉ እና ጭካኔ የተሞላባቸዉ ጥናቶችን አለማችን አስተናግዳለች።
የምርምር ስነምግባር በኢትዮጵያ
በሀገራችን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካባቢ የሚደረጉ ጥናቶችን በተመለከት ብዙ ታታሪና ጎበዝ ተመራቂዎች ያሉትን ያህል በርካታ አሳሳቢ ጉዳዮች ይነሳሉ። የመመረቂያ ፅሁፎች ተመሳስለዉ የሚባዙበትና የሚሸጡበት ሁኔታ ፣ ቀድመዉ ከተሰሩ ጥናታዊ ፅሁፎች ከከፊል ወይም በአብዛኛዉ እየገለበጡ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስገባት ፣ የኢነተርኔት ወይም የአርቴፊሻል ኢንተሊገንስነ በመጠቀም የመመረቂያ ፅሁፎች መፃፍ እና አለፍ ሲልም ለራሳቸዉ ለመምህራኑ ገንዘብ እየሰጡ ፅሁፎችን ማፃፍና እራስ እንደሰሩ አስመስሎ ማቅረብ ጥቂቶቹ ናቸዉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች መመረቂያ ጊዜ በደረሰ ቁጥር ገበያ የሚደራላቸዉ የኮሌጅ መምህራን በርካታ እንደሆኑ መስማት ተስፋ የሚያስቆርጥም የሚያበሳጭም እየሆነ ከመጣ ዉሎ አድሯል።
የማህበረሰብን እዉቀትና ባህልን ማክበርና ያላግባብ ለራስ ጥቅም አለማዋል ወይም የራስ አስመስሎ አለማቅረብ
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማቶቻችን ጥናቶችና ምርመሮች በተጨማሪም በተለያዮ የምርምር ተቋማት እንደ ህክምና ስህተቶች ፣ አካባቢን በኬሚካል መበከል ፣ የማህበረሰብን እዉቀትና ባህልን ማክበርና ያላግባብ ለራስ ጥቅም አለማዋል ወይም የራስ አስመስሎ አለማቅረብ፣ ብዝሃ ህይወትን የመያዉኩ ተግባራትንም ልናስተዉል እንችላለን።
በኢትዮጵያበጤና ፣ በግብርናና በአካባቢ ጥናት ዙሪያየምርምር ሰራዎች ከተጀመሩ በረካታ አመታትነ ቢያሰቆጥሩም የምርምር ስራዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ በማቀናጀትና ሥነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ እንዲመሩ በማድገግ እረገድ ያለዉ እንቅስቃሴ የተጀመረዉ በቀርቡ መሆኑን የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ።
በተለይም ከ1995 ዓ.ም. ወዲህ በሀገራችን የታዩትን ለዉጦች የከትሎ የምርምር ስራዎችን ከብሄራዊ ደረጃ አንስቶ እስከ ክልሎች የታችኛዉ አካላት ድረስ የሚደርስ አሰራር ለመዘርጋት ተሞክሯል።
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስትራቴጅ መዉጣትን አሰከትሎ በየተቋሙ የብሔራዊ የምርምር ሥነ-ምግባር ኮሚቴዎች ተቋቁመዉ በርካታ ሥራዎችነ ማከናወን ችለዋል። በዚህም በሰው ልጅ፣ እንስሳትና አካባቢ እንዲሁም በሥነ-ምህዳር ላይ በምርምር ስራዎች ምክንያት ተፅዕኖ እንዳይደርስ በመሰራት ላይም ይገኛል።
ምክንያቱም የሀገራችን የምርምር ተግባራትም በአለማቀፍ ደረጃ እየመጡ ባሉ እድገቶችና ለዉጦች ተፅዕኖ ስር እየወደቀ መሆኑ ይታመቃል። በዘመናችን እየመጡ ባሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ምክንያት የሚያጋጥሙ የሥነ ምግባር ተግዳሮቶች በርካታ ሲሆኑ ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የተያያዙ የሥነ ምግባር ችግሮች ፣የግለሰቦች የመረጃ ነፃነት ጉዳይ፣ አካባቢን ዘላቂ በሆነ መንገድ ከመጠበቅ አንፃር ያሉ ተግዳሮቶች ፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ምክንያት የሚመጡ የጤና ችግሮች እና መረጃን በጦር መሣሪያነት መጠቀምን ጨምሮ ሌሎችንም የሚያጠቃልል ነዉ።
የሕፃናት ዲዛይን ⁄Designer babies⁄
በዚህ ዘመን እየመጡ ካሉ አዳዲስ የምርምር ዉጤቶች መካከል የሕፃናት ዲዛይን ⁄Designer babies⁄ አንዱ ሲሆን የሚሰራዉም “በቅድመ-ኢምፕላንት ጄኔቲክ ምርመራ” (PGD) ወይም በጄኔቲክ ምህንድስና የተሻሻሉ ልጆችን ባህሪያት ላይ ለዉጥ ለማድረግ የሚሰራ የምርምር ስራ ነው። የዚህ ምርምር ዋና ዓላማ በዲ ኤን ኤ ላይ ለዉጥ በማድረግ ወይም በሚውቴሽን አሰራር በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች ከመከላከል ጀምሮ በሚወለዱ ህፃናት ላይ የሚፈለገዉን ለዉጥ የማድረግ ስራ ነው።
ነገር ግን፣ በአመናችን በዚህ የጂን አርትዖት ስራ ላይ ያለዉ እውቀት በቂ አይደለም። በተጨማሪም፣ የሕፃናት ዲዛይን ለመፍጠር እነዚህን ቴክኖሎጂዎች መተግበር አለብን በሚለው ላይ የሥነ ምግባር ስጋቶችና ጥያቄዎች አሉ።
የምርምር ፈንድ አጠቃቀም ግልጽነትና ተጠያቂነት
በሳይንሳዊ ምርምር የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ ፣ ግልጽነት እንደ መሰረታዊ የሥነ-ምግባር መርህ ሆኖ ያገለግላል። የገንዘቦችን አመጣጥ እና አመዳደብ ለመግለፅ ግልጽነት እና ታማኝነት እንደሚያስፈልግ እሙን ነዉ። ከዚህ አስገዳጅነት በስተጀርባ ያለው ምክንያት ዘርፈ ብዙ ነው እና በሁለቱም የገንዘብ ምንጮች እና በሳይንሳዊ ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን የሃብት ስርጭት በግልጽነት እና በተጠያቂነት ማከናወን ያሰፈልጋል።
የግለሰቦች መብት
በምርምር ስራ ዙሪያ ያሉ የሥነ ምግባር ችግሮች መካከል ከግለሰቦች መብት አጠባበቅ ጋር የተገናኙ ናቸዉ። የግለሰቦች መብት ስጋቶች በሁሉም የምርምር ደረጃዎች ላይ ይከሰታሉ፣ እነዚህም የመጀመሪያ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ የጥናት ጥያቄዎችን በመፍታት አጠቃቀም ዙሪያና እና ትንተና፣ ግኝቶችን በማሰራጨት፣ መረጃን በማከማቸት እና ማቆየት እና መረጃ የተከማቸባቸው መዝገቦች ወይም መሳሪያዎች በማስወገድ ስራዎች ሁሉ ያሉ ሂደቶችን ይመለከታል።
በዘመናችን እየመጡ ባሉ አዳዲስ የምርምር ስራዎች ዙሪያ ከሚከሰቱ የሰነምግባር ችግሮች መካከል የግለሰቦች መብት ጥሰትን የተመለከተ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ ጥሰት እነዳይከሰት መሰራት ይኖርበታል።
በአንጎል ላይ የሚገጠም ችፕስ ⁄Neuralink’s human trials⁄

በዘመናችን በአሜሪካዊዉ ቁንጮ ባለሀብትና የቴክኖሎጂ ፈጣሪዉ ኤለን መስክ አነሳሽነት በአዕምሮ ላይ የሚገጠም የኮምፒዩተር ችፕስ ⁄ኒውራሊንክ⁄ ን በሰዎች ላይ በሚደረገዉ ሙከራ ዙሪያ የስነምግባር ስጋቶችን ይነሳሉ። እነዚህ የስነምግባር ስጋቶች የኒውራሊንክን ጥረቶች እና የአዕምሮ-ኮምፒዩተር መገናኛዎች ሰፊ አንድምታዎችን አስከትለዋል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ኒውራሊንክ እ.ኤ.አ. በ2018 በእንስሳት ላይ ሙከራ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ1,500 በላይ እንስሳት ሞተዋል። በዚሁ ምክንያት ሰፊ የስነምግባር ስጋቶች እየተነሱ ይገኛሉ።
በዘመናችን በአሜሪካዊዉ ቁንጮ ባለሀብትና የቴክኖሎጂ ፈጣሪዉ ኤለን መስክ አነሳሽነት በአዕምሮ ላይ የሚገጠም የኮምፒዩተር ችፕስ ⁄ኒውራሊንክ⁄ ን በሰዎች ላይ በሚደረገዉ ሙከራ ዙሪያ የስነምግባር ስጋቶችን ይነሳሉ
ከነዚህ ለምሳሌ ከተጠቀሱ የምርምር የሥነ ምግባር በተጨማሪ የማህበረሰብን እምነት ፣ ባህል ፣ ቋንቋ፣የአኗኗር ዘዴ ፣ እውቀትና መረጃን እንዲሁም የተፈጥሮ ሀብት ላይ ችግር የማያደርስ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
በተለይም በሀገራችን በምርምር ስነምግባር ዙሪያ በአርቴፊሻል ኢነተሊጀንስ ⁄Artificial intelligence⁄ እና ማህበረሰብን ከማሳተፍ አንፃር በርካታ ስራ መሰራት እንዳለበት ይነገራል።
ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ሲባል በሀገራችን የሚካሄዱ ምርምሮች ለሀገርና ለዜጎች ይበልጥ ጥቅም እንዲሰጡ ለማስቻል ሀገር አቀፍ የምርምር ሥነ-ምግባር መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በሌሎች የምርምር ተቋማት የምርምር ሥነ-ምግባር እየተዘጋጀ፣ የምርምር ገምጋሚ ኮሚቴዎችም እየተቋቋሙ የምርመር ስራዎች ሥነ-ምግባር ያሟሉ እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ በምርምር ዙሪያ የሚከሰቱ የህግ ጥሰቶችን ለመከላከል በርካታ ህጎች የመጡ ሲሆኑ መሻሻል ያለባቸዉንም በማሻሻልና አዳዲስ መዉጣት ያለባቸዉንም በማዉጣት ለምርምር ስራ ስነምግባር መከበር መስራትም ያስፈልጋል።
ይሁንና በሀገራችን ከላይ የተጠቀሱት በዘመናችን እየመጡ ያሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂና ዉጤቶቻቸው በጤና ፣ በግብርናና በአካባቢ ጥናት የምርምር ወቅት ስለሚተገበሩና ተመራማሪዎች ላይ የተለያዩ ተፅእኖዎችን ማሳረፋቸዉ ስለማይቀር የምርምር ስነምግባርን ⁄ Research Ethics ⁄ ማስፈንና ተጠያቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
