
ባህርዳር፣ ህዳር 21 ፣2018 ዓም — በአማራ ክልል ከሰባት አመት ዕድሜ በታች ያሉ ሕፃናትን የቀዳማይ ልጅነት የእድገት ሁኔታ ለማሻሻል አጋር አካላት በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ።
ጥሪዉ የቀረበዉ የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዛሬ በባህር ዳር ከተማ በአማራ ክልል የቀዳማይ ልጅነት ልማት ላይ ያተኮረ የመነሻ የዳሰስ ጥናት ዉጤት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነዉ።
የቀዳማይ ልጅነት ልማት መልካም ጤንነትን፣ የቀዳማይ ልጅነት የመማር ዕድልን፣ ደህንነትና እና ጥበቃን፣ በቂና የተመጣጠነ ምግብ እና ምላሽ ሰጪ እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግን ያጠቃልላል።
ጥናቱ ጨዋታን መሰረት ያደረገ የቀዳማይ ትምህርት እድልን፣ የጤናና የስርአተ-ምግብን ፣ የህፃናትን ጥበቃና ከለላን እና ልሎች አስፈላጊ የሆኑ መለኪያዎችን ጨምሮ በህፃናት ልማት ውጤቶች ላይ ያተኮረ ነዉ።
ጥናቱ ለክልሉ በአይነቱ የመጀመሪያና ሁለንትናዊ ሲሆን የአለም አቀፍ መስፈርቶችን በመከተል የተሰራ ነዉ።
የዳሰስ ጥናት ዉጤት ይፋ የተደረገበትን ስብሰባ በክብር እንግድነት ተገኝተዉ የከፈቱት ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የክልላዊ ማህበራዊ ልማት ክላስተር መሪ እንደተናገሩት እስከዛሬ በሀገራችን የምንከተለዉ የእናቶችና የህፃናት ክብካቤ በመሰረቱ መቀየር እንዳለበትና የቀዳማይ ልጅነትን ሳይንስ የተከተለ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል።
እንደ ዶ/ር ሙሉነሽ የቀዳማይ ልጅነት ልማትን ለማረጋገጥ ማህበረሰብን በማሳተፍ እያንዳንዱ ልጅ ሙሉ አቅሙ ላይ ለመድረስ እድል እንዲኖረው መስራት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በቀዳማይ ልጅነት ልማት አመርቂ ተሞክሮ ከቀመረዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ብዙ መማር የሚቻል መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለተደረገዉም የመነሻ የዳሰስ ጥናት የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከልን እና የአማራ ክልል ቢሮዎችን እና ሌሎች አስተዋፅኦ ያበተከቱ አካላትን ሁሉ አመስግነዋል።

የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ከበደ ወርቁ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በበኩላቸዉ ሲናገሩ ይፋ የተደረገው የመነሻ ዳሰሳ ጥናት በክልሉ ውስጥ ያሉ ሕጻናት ጤና፣ ደህንነት፣ ትምህርት እና ሁሉን-አቀፍ ልማትን ለማሻሻል የምናደርገውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያጠናክር ቁልፍ እርምጃ ነው ብለዋል።
“የጥናቱ ውጤት በመረጃ ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ለመቅረጽ እና ለልጆች የወደፊት ዕድልን ለማሻሻል ዋና መሠረት ሆኖ ያገለግላል። ጥናቱ በክልሉ ውስጥ ያለውን የቀዳማይ ልጅነት ሁኔታ በጥልቅ የሚገልጽ መረጃ ይሰጠናል።”
“የጥናቱ ቁልፍ ግኝቶች በረቂቅ ያለውን የክልሉን የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፍኖተ-ካርታ ለማጥራት፣ ለመተግበር እና ለመከታተል ጠንካራ መሠረት ሆኖ ያገለግላል። ክልሉ የቅድሚያ ትኩረት የሚሰጣቸውን ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን ለማስቀመጥ፣ ለውጦችን ለመለካት እና ለህጻናትና ቤተሰቦች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ያግዘዋል።”
እንደ ዶ/ር ከበደ ከሆነ በፍኖተ-ካርታው ከጽንስ ጀምሮ እስከ 6 ዓመት ያሉ ልጆች መልካም ጤንነት፣ ቀዳማይ የመማር ዕድል (የቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርትን ጨምሮ)፣ በቂና የተመጣጠነ ሥርዓተ-ምግብ፣ ደህንነትና ጥበቃ፣ እና ምላሽ ሰጪና አነቃቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያረጋግጡ ዋና ዋና ግቦች ተቀምጠዋል።
እነዚህም የቀዳማይ ልጅነት ልማት አገልግሎቶችን በጤና አጠባበቅ ስርዓት ውስጥ ማቀናጀት፣ ለወላጆችና አሳዳጊዎች የቤት-ለቤት ምክርና ስልጠና መስጠት፣ ዶ/ር ከበደ ብለዋል።
ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር ያተከናወነ ሲሆን የቀዳማይ ልጅነት ዕድገት በምን ደረጃ እና ሁኔታ ላይ እንዳለ ያመለከተና ለዉሳኔ ሰጪዎች ተጨባጭ መረጃ ለማድረስ ታስቦ የተሰራ ነዉ፡፡
የማዕከሉ ከፍተኛ የምርምር አማካሪ ዶ/ር ስንታየሁ አባተ እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ነፃነት ፋንታሁን ስለጥናቱ ዉጤት በዝርዝር ለተሳታፊዎች ገለፃ ሰተዋል።
ዶ/ር ስንታየሁ በወቅቱ እንዳስረዱት ጥናቱ በአማራ ክልል ያሉ የዞን ከተሞችን እና በዙሪያቸዉ ያሉትን ገጠራማ ወረዳዎች በስድስት ክላስተር በማድረግ የዳሰሰ ነዉ እንደሆን ተናግረዋል ።

በአማራ የሚኖሩ ህጻናት እድገታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ በርካታ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ የቀዳማይ ትምህርት ተደራሽነት ውስንነት፣ ዝቅተኛ የወላጅ ትምህርት ደረጃ እና የዘርፎች ግንኙነትና ቅንጅት ዝቅተኛ መሆን ለልጆች እድገት እንቅፋት ሆኖ
ዶ/ር ስንታየሁ አክለዉም ከ3 ዓመት በታች ካሉ የክልሉ ሕፃናት 21.7 በመቶዉ ከሚጠበቀው የአእምሮ እድገት ደረጃ በታች ናቸው። ይህ በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚጠበቀዉ ዝቅተኛ መመዘኛ ማለትም 5% ጋር ሲነፃፀር በአራት እጥፍ ከፍ ያለ እንደሆነ ጥናቱ ያሳያል ብለዋል፡፡
የሕፃናት የእድገት ሁኔታ በክልሉ ገጠራማ ቦታዎች በ23.1% ዝቅ ያለ ሲሆን እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸዉ ቤተሰቦች ደግሞ በ26.7% ዝቅ ያለ ነዉ።
ከ6,000 በላይ ተሳታፊዎች በዚህ ጥናት የተካተቱ ሲሆን ከሰባት ዓመት በታች ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦችን እንዲሁም ከ4–6 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን የቀዳማይ ትምህርት የሚከታተሉ ሕፃናት ላይ አተኩሮ የተሰራም ነዉ።
በፕሮግራሙም የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር ዘርፍ ፣ የጤና፣ የትምህርት እንዲሁም የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች የተሳተፉበትና በማዕከሉ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር መሰረት ዘላለም አወያይነት የፓነል ዉይይም የተካሄደ ሲሆን በክልሉ የቀዳማይ ልጅነት ያለበትን ሁኔታና መሰራት ያለባቸዉን ተግባራት ላይ ያተኮረመም ነበር።
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመሰከረላቸዉን የምርምር ዘዴዎች በመጠቀም የቀዳማይ ልጅነት አገልግሎት ጥራትን፣ የህፃናትን ተንከባካቢዎችንና ወላጆችን ሁኔታዎችን ጨምሮ ሁለንተናዊ እድገታቸዉን ሰሱበትም ነዉ።
የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ጥናቱን ለማካሄድ ከቢግ ዊን ፊላንትሮፒ /Big Win Philanthropy/ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ያገኘ ሲሆን ጥናቱንም ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በትብብር አከናዉኗል ።
