በመኮንን ተሾመ

በ 5 ተከታታይ የዝናብ እጥረትና የድርቅ ወቅቶች ምክንያት በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝለት ሰብአዊ ውድመት አጋጥሞናል። አሁንም 6ኛው የዝናብ እጥረት እንደገና ይጠበቃል ሲል ICPAC አስጠንቅቋል።
በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን በተከሰተው ድርቅ ከ800,000 በላይ ሰዎችን ህይወት አደጋ ላይ መውደቁን እና ከ2 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ የቤት እንስሳቶች በተፈጥሮ አደጋ መሞታቸውን የመንግስት ቴሌቪዢንን ጨምሮ ምንጮች አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት በዞኑ ውስጥ ላለፉት አምስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ባለማግኘታቸው በውሃ እጦት እየተሰቃዩ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለረሃብ ስጋት ያጋለጠው ሁኔታ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ያስፈልገዋል ተባለ።
በአካባቢው ከብቶች የከፋ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ800,000 በላይ ሰዎች አስቸኳይ እርዳታ እንደ ምግብ፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እና የህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿዋል።
በኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ 23 ሚሊዮን ሰዎች “በከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት” ላይ እንዳሉ ተዘግቧል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትን ሞተዋል፣ ሰብሎች ወድመዋል እና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸው የፈናቅለዋል።
ይህ እየከፋ፣ ከየካቲት 2023 ጀምሮ፣ በመጪው መጋቢት-ግንቦት ወር ከአማካኝ በታች እንደሚሆን ይጠበቃል ሲሉ በአላም አቀፍ ኤጀንሲዎች የተለቀቀው የጋራ መግለጫ እና ሌላዉ የREACH ዘገባ አሳይቷል።
እአአ 2023 ማርች – ሜይ ዝናባማ ወቅት ትንበያዎች “የተዛባ የዝናብ መጠን እና ከፍተኛ ሙቀት” እንደሚያመለክቱ የመንግስታቱ ድርጅት የልማት የአየር ንብረት ትንበያ ማእከል (ICPAC) በዚህ ሳምንት ተናግሯል።
“በቅርብ ጊዜ በተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት ባጋጠማቸው የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ኡጋንዳ ክፍሎች ይህ ለ6 ተከታታይ ጊዜ ዝናብ ያልተሳካ ሊሆን ይችላል” ሲል አይሲፒኤሲ በመግለጫው ገልጿል። በናይሮቢ የሚገኘዉ ICPAC በአለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአየር ንብረት ማዕከል ነው።
እ.ኤ.አ. የካቲት 16 ቀን 2023 ባወጡት መግለጫ የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት (WMO)፣ የምግብ እና ግብርና ድርጅት፣ የረሃብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ኔትወርክ (FEWS NET) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ሁኔታዉን ግለፅ አድርገዋል።
ምስራቅ አፍሪከ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለሶስት ዓመታት የዘለቀ ድርቅ ገጥሞት ማህበረሰቡ አፋጣኝ እርዳታ እንዲያገኝ አድርጓል። በአፍሪካ ቀንድ ሶስት ሀገራት – ኬንያ፣ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ – ከ 2020 መጨረሻ ጀምሮ ቀጣይነት ያለው ድርቅ እያጋጠማቸው ነው።
የአሁኑ ድርቅ የጀመረው በጥቅምት – ታኅሣሥ 2020 የዝናብ እጥረት በማጋጠሙ ነበር። በመጋቢት – ግንቦት ያለው የዝናብ መጠን ከመደበኛ እና ከመደበኛ በታች ይሆናል ተብሎ የተገመተ ሲሆን ከመደበኛው በላይ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው ሲሉ የአየር ንብረት ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
ይህ ምን ማለት ነው?
ሌላው ከመደበኛ በታች የዝናብ መጠን እንደሚያመለክተው ክልሉ ለ6ተኛ ተከታታይ ድርቅ መዘጋጀት እንዳለበት ነው። በታሪክ፣ ይህ በ2022 ከተመዘገበው በአፍሪካ ቀንድ ረጅሙ የደረቅ ወቅቶች ሊሆን ይችላል።
እ.ኤ.አ. በ2022 የጣለው ረዥም ዝናብ (ከመጋቢት – ግንቦት ወቅት) ከ73 ዓመታት ወዲህ አስከፊነቱ የታየበት ነዉ። በ REACH በተለቀቀው ክልላዊ ትንታኔ መሰረት የዚህ አመት ወቅትም እንዲሁ ሊሆን ይችላል.
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየጨመረ የመጣውን የሙቀት መጠን እና ኤልኒኖን ጨምሮ የተለዋዋጭ አየር ለድርቁ አስተዋፅዖ አድርገዋል ሲል የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ ኤሮናውቲክስና የጠፈር አስተዳደር አስታዉቋል።
የኤልኒኖ ተጽእኖ?
በ2023 ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ኤልኒኖ የመፈጠር እድል ከ50 በመቶ በላይ መሆኑንም ዳውን ቱ እርዝር ዘግቧል።
ትንበያው እውን ከሆነ በሰኔ – መስከረም መጨረሻ አካባቢ ባሉት ደጋማ ቦታዎች፣ በኬንያ፣ በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን ደጋማ አካባቢዎች የዝናብ መጠን እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል።
የሰብአዊ ቀውስ
በዝናብ እጥረት ሳቢያ የብዙ ዓመታት ድርቅ ያስከተለው አስከፊ መዘዝ እስከ 2023 እንደሚቀጥል ኤጀንሲዎቹ አስጠንቅቀዋል፣ ዳውን ቱ እርዝ እንደዘገበው።
አሁን ያለው ድርቅ በምግብ ዋስትና እና በኑሮ ላይ እንዲሁም በውሃ አቅርቦት፣ በንፅህና እና በንፅህና አጠባበቅ ላይ እያሳደረ ያለው ተጽእኖ ሰፊ ነው።
በጃንዋሪ 2023 ከ22.5 እስከ 23.4 ሚሊዮን ሰዎች በዋነኛነት በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና በሶማሊያ ድርቅ ሳቢያ ለከፋ የምግብ ዋስትና እጦት ተዳርገዋል።
በኬንያ በ32 አውራጃዎች ውስጥ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በተራዘመው ድርቅ እና ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጎጂ ሆነዋል። የኬንያ ብሄራዊ ድርቅ እና አስተዳደር ባለስልጣን በዚህ ሳምንት ይፋ ባደረገው ዘገባ መሰረት ሁኔታው በተለይ ደረቃማ እና ከፊል ደረቃማ ተብለው በተመደቡት አውራጃዎች ውስጥ በጣም አስከፊ ነው።
በአሁኑ ወቅት በድርቅ በተጠቁ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢዎች በአጭር የዝናብ ወቅት (በጥቅምት እና ታኅሣሥ መካከል) ብዙ ዝናብ ሊኖር ይችላል።በአጭር ጊዜ ውስጥ የጣለ ከባድ ዝናብ ተጨማሪ ጎርፍ እና የውሃ ወለድ በሽታዎች ሊያመጣ ይችላል ተብሏል። ስለዚህ አሁን ያጋጠመንን የድርቅ አደጋ እየተከላከልን ለመጭዉ ጊዜም መዘጋጀት ይኖርብናል።
