
የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ግጭት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጻናት እየሞቱ መሆኑን ገለፀ። እንደ ዘገባው ከሆነ በየሰዓቱ ሰባት ህጻናት ይገደላሉ ወይም ይጎዳሉ ።
እንደተፈራው የሱዳን ሁኔታ እጅግ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ህጻናትን ገዳይ ሆኗል። ዩኒሴፍ ባገኘው ዘገባ መሰረት ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ኤፕሪል 25 ቀን 2023 ባለዉ ጊዜ 190 ህጻናት ተገድለዋል። በሁከቱ ምክንያት ቁጥሩን ማረጋገጥ ባንችልም ከእነዚህ ዘገባዎች ተጨማሪ 1700 ቆስለዋል ብሏል ሲሉ ተ∙መ∙ድ∙ ሀላፊዎች አሰረድተዋል።
ይህም ማለት በአማካይ በየሰዓቱ በዚህ የመጀመሪያ 11 ቀን ጦርነት ሰባት ህፃናት ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል የሚሉ ሪፖርቶች አሉን።
እነዚህ የተገደሉ ወይም የተጎዱ ህፃናት ሪፖርቶች ከህክምና ተቋም የተገኙ ብቻ ሲሆን እውነታው ግን በጣም የከፋ ሊሆን ይችላል። በካርቱም እና በዳርፉር ግጭት በተከሰተባቸው ቦታዎች የተገኘው መረጃ ቢሆንም ስለእያንዳንዱ ህፃን ሁሌታ የሚያሳይ አይደለም።
እነዚህ ዘገባዎች የዚህን ግጭት የመጀመሪያዎቹን 11 ቀናት ብቻ የሚሸፍኑ ቢሆንም፣ አሁን በሱዳን ውስጥ ህጻናት ለሶስት ሳምንታት በአስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ናቸዉ። በቀላሉ ደህንነታቸው ሊጠበቅ የሚገባቸዉ ቦታዎች – ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች – ያለማቋረጥ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። ዩኒሴፍ እና አጋሮቹ በግጭቱ ውስጥ ያሉ ወገኖች በጤና ጣቢያዎች፣ ትምህርት ቤቶች እና ህጻናት በሚተማመኑባቸው የውሃ እና የንፅህና አጠባበቅ ስርዓቶች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ጥቃት እንዲያቆሙ ደጋግመው ጥሪ አቅርበዋል። ይሁንና ጥቃቱ አሁንም ቀጥሏል።
“የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችም ጥቃት ደርሶባቸዋል፣ የሰብአዊ ተቋማት ተሽከርካሪዎች እና አቅርቦቶች – የዩኒሴፍን ጨምሮ – ተዘርፈዋል ወይም ወድመዋል። እነዚህ ሁሉ ጥቃቶች በመላ ሀገሪቱ ህይወት አድን የጤና፣ የተመጣጠነ ምግብ፣ የውሃ እና የንፅህና አገልግሎት ለህጻናትን የማድረስ የማይቻልበት ሁኔታነ ፈጠረዋል። አሁንም፣ በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት አለም አቀፍ ህግን አክብረው፣ ህጻናትን የመጠበቅ ግዴታቸውን ለመወጣት እና የሰብአዊነት ተዋናዮች የተቸገሩትን ሲቪሎች ለመደገፍ እንዲችሉ ለማድረግ ወሳኝ በመሆኑን ይህዉ እንዲረጋገጥ እየሰራን ነዉ።“ ሲሉ ተ∙መ∙ድ∙ ሀላፊዎች ተናግዋል።
