
በመኮንን ተሾመ
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ – የአሜሪካ ብሔራዊ የውቅያኖስና የከባቢ አየር አስተዳደር (NOAA) ተቋም ባለፈዉ ሳምንት እ.አ.አ በጥር 9፣ 2025 በፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢ እንደገና የላ ኒና (La Niña) ክስተት አመላካች መታየቱን እና ይህም በዚህ አመት ከፍተኛ የዉቅያኖስ ቅዝቃዜና በአለም ዙሪያ የድርቅ ክስተቶችን የሚያመጣ መሆኑን ገልጿል ።
ላ ኒና (La Niña) እና ኤል ኒኖ (El Niño)
የላ ኒና (La Niña) ክስተት የኤልኒኖ ሳውዝ ኦስሲሌሽን (ENSO) ተብሎ የሚታወቀዉ ሂደት አካል መሆኑን የተቋሙ ባለሞያዎች ተናግረዋል። ክስተቱም በማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ፓሲፊክ አካባቢ ከመደበኛው የበለጠ ቀዝቃዛ የሆነ የአየር ሁኔታ ሲከሰት የሚፈጠር ሲሆን ይህም ከፍተኛ ቅዝቃዜና የአውሎ ንፋስ እንዲሁም በአንዳንድ የአለማችን ክልሎች ከመጠን በላይ የሆነ የዝናብ ሁኔታዎች የሚያመራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኤል ኒኖ (El Niño) ክስተት ደሞ የላ ኒና ተቃራኒ ሆኖ በማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ፓሲፊክ ከመደበኛው የበለጠ ሞቃት የሆነ የአየር ሁኔታ ሲከሰት የሚፈጠር ነው ሲሉ ባለሞያዎች ይናገራሉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ ወደ በአነፃሩ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ሞቃታማ የአየር ሁኔታዎችን ፣የሙቀት ማዕበልን እና የሰደድ እሳትን ሊያስከትል ይችላል።
የላ ኒና (La Niña) ክስተት እና ተፅዕኖዉ
“ይህ ክስተት በተለምዶ በአንዳንድ ክልሎች የዝናብ መጠን መጨመር እና በሌሎች ደግሞ ድርቅን ያስከትላል። የላ ኒና ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ ሞቅ ያለ ውሃን ወደ ምዕራብ ፓስፊክ ከሚገፋው በጠንካራ ንፋስ በመታገዝ ነዉ።” ሲልም የውቅያኖስና የከባቢ አየር አስተዳደሩ አክሏል።
እንደ ኤክስፐርቶቹ ገለፃ ከሆነ አሁን ያለዉ የውቅያኖስ ሞቅታ መጠን እረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል የላ ኒና መከሰቱም ሂደት ሊዘገይ እንደሚችል ተጠቁሟል።
“ይህ ሂደት በባህር ወለል ሙቀት እና በከባቢ አየር መካከል ያለውን ግንኙነት ያካትታል። በኤል ኒኖ ወቅትም ደካማ የምስራቅ የንግድ ንፋስ በፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢ የሞቀ ውሃ እንዲከማች ያደርጋል። በተቃራኒው፣ በላ ኒና ወቅት ጠንከር ያለ የንፋስ ሁኔታ የቀዝቃዛ ውሃን መጠን ይጨምራል። በእነዚህ ክስተቶች ሁኔታም ላይም በቀጣይነት የምርምር ስራ መሰራተ ይኖርበታል።”
እንደ ባለሞያዎቹ ከሆነ የኤል ኒኖ (El Niño) እና የላ ኒና (La Niña) ክስተቶች በመላዉ አለማችን በተለይም ደግሞ በፓስፊክ ውቅያኖስ አዋሳኝ ታዳጊ ሀገራት ውስጥ በሚደረጉ የእርሻ እና የአሳ ማጥመድ ስራዎች ላየ ተፅእኖዉ ጎልቶ ይታያል።
ክስተቶቹም ለአንድ አመት ያህል የአለምን የሙቀትና የቅዝቃዜ ሁኔታ ሊወስኑ ይችላሉ። በአለማችን የመጨረሻዉ ላ ኒና የተከሰተዉ እ.አ.አ. በ2020 እስከ 2023 ነው።
እስካሁን የተደረጉት የባለሞያዎች የአየር ንብረት የጥናት ሞዴሎች እንደሚያመለክቱት ይህ ዑደት ከአለም ሙቀት መጨመር ምክንያት እንደ ድርቅ ፣ ከፍተኛ ቅዝቃዜናየአውሎ ንፋስ የተፈጥሮ በአደጋዎች ሊከሰቱ ይችላል።
የቅድመ ዝግጁነትና የአደጋ መከላከል ስራ
በመሆኑም አገራት ይህንን የባለሞያዎች ትንበያ መነሻ በማድረግ የአደጋ መከላከል የቅድመ ዝግጁነት ስራ ሊሰሩ ይገባል። አገራዊ እቅድ ተላሚዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የተለያዩ ዘርፎች ተመራማሪዎች የሁኔታዎች ግምገማና የወደፊት ክስተቶችን የመተንበይ ዘዴ ተጠቅመዉ ስራቸዉን መስራት ይኖርባቸዋል ተብሏል።
አሁን ያለውን ሁኔታ በመተንተን ፣ ስለወደፊቱ ጊዜ /Scenario Development/ በመረጃ የተደገፈ ግምቶችን በመፍጠር ፣ ሊኖሩ ስለሚችሉት ተፅእኖ ማስቀጥ እና የተለያዩ ተዋናዮችም በማሳተፍ ሊኖሩ በሚችሉ ምላሾች ላይ መስራትም ይገባል።
