By African Demystifier

ለቀጣዮቹ ሳምንታት በኢትዮጵያ የመካከለኛው የስምጥ ሸለቆ ክልሎች ቀለል ያለ የዝናብ መጠን የሚመዘገብ ቢሆንም አጠቃላይ ሁኔታው አሁንም በአካባቢው ከመደበኛው የዝናብ መጠን በታች ሆኖ እንደሚቆይ የአየር ንብረት ትንበያ ጠቁሟል።
የአፍሪካ ፋሚን ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሲስተምስ ኔትወርክ እና ዩ∙ኤስ∙ኤ∙አይ∙ዲ በጋራ ባወጡት ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ እ∙አ∙አ በየካቲት 2023 ሶስተኛ ሳምንት ውስጥ አብዛኞቹ ቦታዎች ደረቃማ ሆነዉ ቆይተዋል።
በተጨማሪም ሰሜን እና ምስራቃዊ ታንዛኒያ በዚህ ሳምንት ትንሽ ዝናብ አግኝተዋል ያለዉ ሪፖርቱ ባለፉት 30 ቀናት ከአማካይ በታች ዝናብ/ ከ10-100 ሚ.ሜ የሚደርስ ጉድለት/ በደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው ኢትዮጵያ፣ ምዕራብ ኬንያ፣ ዩጋንዳ እና አብዛኛው ታንዛኒያ ቀጥሏል ሲል አክሏል።
ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ደረቃማ ሆኖ የቆየዉ አካባቢዉ የዝናብ ጉድለቶቹም ከ 50 ሚሊ ሜትር በላይ እየጨመረ በመምጣቱ በደቡብ ምዕራብ ኬንያ ያልተለመደ ደረቅነት አሳይቷል ሲል ገልፆ በክልሉ ባለፈው አመት የዝናብ ወቅትም በጣም ደካማ ዝናብ ነበር ሲል ገልፆል።
በሪፖርቱ መሰረት፣ ኢትዮጵያ በዚህ የበልግ ዝናብ ወቅትም እርጥበት ያለዉ አየር ያነሰ የመሆን አዝማሚያ ይቀጥላል ብሏል። “ይህም ቀድሞውንም በደረቃማዉ ወቅት አሉታዊ ተፅእኖ ያረፈባቸዉን የእፅዋትን ዉሱኑነትና የውሃ እጥረት ሊያጠናክር ይችላል ” ብሏል።
