
በመኮንን ተሾመ ቶሌራ (ከአፋር፣ ሰመራ )
ቴምር – ሌላው የአፋር ክልል ፀጋ
የቴምር ዛፍ በበርሃማ አካባቢዎች የሚበቅልና ለምግብ ዋስትና፣ ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት መቀነስ፣ ለአርሶ አደሮች ገቢ መጨመርና ለድህነት ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ፍራፍሬ ነዉ።

የቴምር ተክል በኢትዮዽያ ለረጅም ዘመናት የሚታወቀ ሲሆን በተለይም በአፋር፣ ድሬዳዋ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ፣ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተለያዩ ቦታዎች በተፈጥሮ እና በሰዉ ሰራሽ መንገድ ለምቶ ይገኛል ። ወደ 96 707 ስኴር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለዉ የአፋር ክልል ደግሞ ከአዋሽ ወንዝ ዉሃ ጋር ተደምሮ ለቴምር ምርት በጣም ተስማሚና ምቹ አድርጎታል።
በመሆኑም ይህንን የክልሉን ተፈጥሮአዊ አቅም የተረዱ ባለሞያዎች ከአመታት በፊት ከእስራኤል እና ከእግሊዝ ሀገር በቲሹ ካልቸር የተባዙና “በርሄ“ እና “ሜጁል“ የተባሉ የቴምር ዝርያዎች በአፋር ክልል በተለይ አፋምቦ እና አሳይሳ አካባቢ በመትከል በዝርያዎቹ ላይ ምርመር ሲካሄድ ቆይቷል።
“እስካሁን የተደረጉ ምርምሮች እንደሚያሳዩት የቴምር ዛፍን በዘር ፍሬ የማባዛቱ ሂደት እረዥም ጊዜን የሚወስድ ሲሆን በግንጣይ /Off-Shooting/ የማባዛቱም ሁኔታ ከምርታማነተና ከበሽታ መተላላፍ ጋር የራሱ የሆኑ ችግሮች ስላሉበት የቲሹ ካልቸር የማባዛት ሂደት የተሻለ ነዉ ተብሎ ታምኖበታል።”
በኢትዮጵያ የአፋር ክልል ለቴምር ተክል ተስማሚ የሆነ ሰፊ የድንግል መሬት መገኛ ነው። ክልሉ በዳናኪል ዲፕሬሽን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ሞቃታማ የአየር ንብረት ያለው ሲሆን የሙቀት መጠኑ እስከ 50 ዲ᎐ ሴ᎐ የሚደርስ ነዉ። በክልሉ የቴምር ፍሬ የሚመረተዉ በዋናነት ለአካባቢው ፍጆታ ነው።
በአፋር ክልል ዋናው የመስኖ ምንጭ ከአዋሽ ወንዝ ነው። የአዋሽ ወንዝ ከኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች ተነስቶ በበርካታ ገባር ወንዞች እየተመገበ የአፋርን በረሃማ መሬቶች በብዛት ያዳርሳል። በአፋር ክልል የቴምር ፍሬ ማምረት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎች አሉት።
የቴምር ልማቱ ማነቆዎች ምንድን ናቸዉ ?
ይሁንና ስራዉ ከተጀመረ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም የታየዉ ለዉጥና እድገት ግን ብዙም የሚያስመካ አይደለም።
በመሆኑም የኢትዮዽያ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት ሰኔ 4፣2016 ዓ᎐ም᎐ በአፋር ክልል በሚገኙት የቴምር ልማቶች ጉብኝት በማዘጋጀት እንዲሁም በማግስቱ ሰኔ 5፣2016 ዓ᎐ም᎐ ደግሞ በሰመራ ከተማ በቴምር ልማትና ምርምር ዙሪያ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር ስብሰባ በማድረግ ቀደም ሲል ተጀምሮ የነበረዉን የቴምር ልማትና ምርምር በመገምገም የሰብሉ ምርታማነት ችግሮችን ለመቅረፍ ድጋፍ መንቀሳቀስ ጀምሯል።
በወቅቱ በኢንስቲዩቱ አሰተባባሪነት ከኢንስቲዩቱ ፣ ከክልሉ ግብርና ቢሮ ፣ ከኢትዮዽያ ግብርና ምርምር ተቋም ፣ ከግብርና ሚኒስቴር ደን ልማት መምሪያ ፣ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት እና ሎሎች ከሚመለከታቸዉ አካላት የተዉጣጡ ባለሞያዎች ጉብኝትና ምክክር ተደርጓል።
አቶ ይታገስ ኩማ የወረር ግብርና ምርምር የፍራፍሬ ምርት ተመራማሪ እንደሚሉት በርሄ እና ሜጁል የተባሉት ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ምርጥ ዝይያዎች በአፋምቦ ፣ አሳይታና ሌሎቹም ቦታዎች ተተክለዉ ወደ ስራ ቢገባም ዝረያዎቹ አዲስ ከመሆናቸዉ ጋር ተያይዞ ፣ ከተተከሉት የቴምር ዛፎች ዎስጥ የወንዴዉ ቁጥር ማነሱ እና ተክሉ በአንድ አመት በጣም ብዛት ያለዉ ምርት ሰቶ በሌላኛዉ አመት ምርት የማይሰጥበት ሁኔታ በመፈጠራቸዉ ውጤቱ እንደተጠበቀው ልሆነም።
እንደ አቶ ይታገስ ከሆነ የተጠቀሱት የዝርያዎቹ ችግሮች እነዳለ ሆነዉ የሚሰጠወት የፍሬ ብዛት እና ምርታማነት በጣም አመርቂ ነዉ።

በባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የእፅዋት ባዮቴክኖሎጂ ተመራማሪ ዶ/ር ዳግማዊት ቾምቤ እንዳሉት የቴምር ምረት አንዴ ከተተከለ ለረጅመ ዘመናት ምርት የሚሰጥና ለአርሶ አደሮች ከፍተኛ ጠቀሚታ ያለዉ (Perennial) ፍራፍሬ ቢሆንም ምርት በመስጠትና በማላመድ ሂዳት የራሱም ተግዳሮቶች ያሉት ተክል ነዉ።
“እስካሁን የተደረጉ ምርምሮች እንደሚያሳዩት የቴምር ዛፍን በዘር ፍሬ የማባዛቱ ሂደት እረዥም ጊዜን የሚወስድ ሲሆን በግንጣይ /Off-Shooting/ የማባዛቱም ሁኔታ ከምርታማነተና ከበሽታ መተላላፍ ጋር የራሱ የሆኑ ችግሮች ስላሉበየ የቲሹ ካልቸር የማባዛት ሂደት የተሻለ ነዉ ተብሎ ታምኖበታል።”
በዚሁ መሰረት በምክክር ስብሰባዉ ወቅት ባለሞያዎቹ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ ሌሎቹም አጋር አካላት የቴምር ዛፍን በቲሹ ካልቸር የማባዛት ስራን በስፋት እንዲያግዙ ጠይቀዋል።
በወቅቱ አረሶ አደሮችን ወክለዉ በምክክር ስብሰባዉ ላይ የተገኙት ሀጂ የሱፍ አሊ እንደተናገሩት የግብይት ሥርዓቶች የተራቀቁ እና በጥሩ ሁኔታ የሚሰሩ አይደሉም።
እሳቸዉ እንደሚሉት የሚመረተዉ ምርተ በክልል ደረጃ አመርቂ ባየሆንም ለተመረተዉም ምርት ቢሆን የዘመናዊ የገበያ ስርአት አለተዘረጋም ።
የመፍትሄ ሀሳቦች
በመሆኑም ተገቢዉን ትምህርት መስጠትን፣ የገበያ ቦታዎችን እና ተቋማዊ ድጋፍን ለማቋቋም መስራትን ፣የተሻሻሉ የቴምር ዝርያዎች ማቅረብን፣ተጨማሪ ሄክታር መሬት ለቴምር ምርት ማዘጋጀትን እና የመሳሰሉት ላይ ለመስራት በቀጣይም ዉይይቱን በጥልቃት ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀይሉ ዳዲ በወቅቱ እንደተናገሩት በክልሉ ያለዉ የቴምር ልማት ለመነሻ ያህል መልካም ቢሆንም ካለዉ ቴምር የማልማት አቅም ሲታይ ግን ገና ብዙ የሚጠበቅ መሆነ ተናግረዋል።
በመሆኑም ኢንስቲዩቱ የቴምር ልማቱን የምርምርና የምርታማነት ችግሮችን ለመቅረፍ ከአጋር አካላት ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ብቻም ሳይሆን ተጨባጭ ዉጤት ለማሳየት ይሰራል።” ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮዽያ የባዮቴክኖሎጂ ማህበር ፕሬዝደንትና የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ፍሬዉ መክብብ በወቅቱ እንዳሉት አፋር ክልል ባለዉ አቅም በመጠቀም የቴምር ምርትን የላቀ ደረጃ ላይ በማድረስ ኢትዮዽያ ከዉጪ የምትስገባዉን ምትር በከፍተኛ ደረጃ መቀነስና የህዝባችንን የስነ-ምግብ ደረጃ ማሻሻል ይገባል።
“እስካሁን በዘርፉ ለነበሩት ተግዳሮቶች ምክንያት በመስጠት ሳይሆን ያለዉ ኣቅም ከፍተኛ በመሆኑ ሁላችንም ተረባርበን አፋር ክልልን በቴምር ምርት ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ማድረስ አለብን።” በማለት ፕሮፌሰር ፍሬዉ አክለዋል።
