
በመኮንን ተሾመ
በልግ 2017 ዓ.ም
(አዲስ አበባ ፣ኢትዮጵያ) – የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ትላንት ጥር 17 ፣ 2017 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ያለፈዉን የበጋ ወቅት ትንበያ ግምገማና እንዲሁም በመጪወቹ አራት ወራት ማለትም ከካቲት እሰከ ግንቦት 2017 ዓ.ም. ያለዉን ደግሞ የበልግ ወቅት የአየር ጠባይ ትንበያ ይፋ አድርጓል።
ኢንስቲትዩቱ በወቅቱ እንደገለፀዉ በመጪዎቹ አራት ወራት ባጠቃላይ የአየር ጠባዩ መልካም የሚባል ቢሆንም ሰፋ ያሉ የሀገራችን ክፍሎች ላይም ከመደበኛ በታች እና በላይ ዝናብ እንደሚኖራቸዉ ይፋ አድርጓል።
የዝናቡ ሁኔታ ከመደበኛ በታች እና በላይ ሆኖ ሲበዛና ሲያንስ የየራሱ አሉታዊ ጎንም እንዳለዉና ሁኔታዎቹ የሚያስከትሉአቸዉን ተፅዕኖዎች በተቀናጀ መልኩ መከላከልና መምራትም እንደሚያስፈልግ ገልፆአል።
ከሚኖሩትም አሉታዊ ተፅዕኖዎች መካከል፣
በግብርና ዘርፍ
ከመደበኛ በታች የዝናብ መጠን በሚኖራቸዉ አካባቢዎች የሰብል ምርትና ምርታማነት መቀነስ ይኖራል፣
የግጦሽ እና የውሃ አቅርቦት መቀነስ እንዲሁም የእንስሳት ተንቀሳቃሽነት እና ሞት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል ። የእንስሳት የጤና መጓደልም ያስከትላል፣
ከመደበኛ በታች ዝናብ በሚኖርባቸዉ አካባቢዎችና ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሰብል መቀነስ አደጋን ይጨምራል፣
በጤና ዘርፍ
በበሽታ አምጪ ተዋሲያን አማካኝነት የሚተላለፉ እንደ ወባ በሽታዎች መከሰት ፣ ለሙቀት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የሚመጣ ጉዳትና እና ከፍተኛ ድካም /Heat Stress and exhaustion/፣
በተለይ ም ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ የእንስሳት በሽታዎች መጨመር ሊታይ ይችላል፣
የሰብሎች እና የግጦሽ መሬት በዉሃ መዋጥ ፣ አንዳንድ የመሠረተ ልማት አውታሮች መንገዶችና የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎችን ጨምሮ በጎርፍ መጎዳት ፣
የኮሌራ ወረርሽኝ (የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የውሃ አቅርቦት እጥረት)፣
በጣም ሞቃታማ በሆኑ አካባቢዎች ደግሞ የሰደድ እሳት መከሰትን ሊያጋጥም ይችላል፣
ሊወሰዱ የሚገባቸዉ የመፍትሄ እርምጃዎች
- የሚጠበቁ የባለብዙ ዘርፍ ተቋማት እርምጃዎችን በአግባቡ ማስተባበርና ማጠናከር
- ለድርቅና ለጎርፍ ተጋላጭ ለሆኑ አካባቢዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ቅድመ ዕርምጃ ስራዎችን መስራት
- ቀድመዉ የሚደርሱ እና ድርቅን የሚቋቋሙ የሰብል አቅርቦት እና ተጠባባቂ የእንስሳት መኖ እንዲዘጋጅ ማድረግ
- ተጨማሪ የእንስሳት መኖ እና የውሃ አቅርቦትን ማሳደግ
- የእንስሳት ክትባት አቅርቦትን ማመቻቸት
- ለተሻለ ህክምና እና የበሽታ አምጪ ተዋሲያን መቆጣጠር የግብአት አቅርቦትና ለማህበረሰብ ንቅናቄ ዝግጁ መሆን
- በታቀደ መልኩ የዉሃና ሳኒቴሽን ስራ ለመስራት የንጽህና መጠበቂያ በአቅራቢያ በሚገኙ የጤና ተቋም እንዲገኙ ማድረግ
- ወባ፣ ኮሌራ እና ሌሎች ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ህመሞችና ወረርሽኞች ስጋት ባሉባቸዉ አካባቢዎች ክትትልን ማጠናከር
- እንስሳት ከመጎዳታቸዉ በፊት እንክብካቤ እንዲያገኙ ማድረግ
- የሚጠበቁ ተግባራትን ለመደገፍ የሀብት ማሰባሰብ ጥረቶችን ማሳደግ
- በወቅቱ ለአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅ በቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶች እና የተሻሻሉ የፍሳሽ መሠረተ ልማት መዘጋጀት
- በውሃ ሃብት እና ባለድርሻ አካላትን በኩል ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ በቅርበት መከታተል
- በሰብል እና በእንስሳት ሁኔታ ላይ ቀጣይነት ያለው ግምገማ ማካሄድ
- የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎች ቅድመ ሁኔታን ማስተካካል
- የአደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማእከላትንን ማጠናከር
- የአደጋ ጊዜ፣ ዝግጁነት እና ምላሽ እቅድ ማዘጋጀት
